ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንትን ተከትሎ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተወስነዋል።
ሊጠናቀቅ የሁለት ሳምንት ዕድሜ የቀረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በትናትናው ዕለት የ28ኛ ሳምንት ጨዋታዎችን አስተናግዶ ጨርሷል። ይህን ተከትሎ የሊጉ ውድድር አመራርና ሥነ-ስርዓት ኮሚቴ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
የመጀመርያው ቅጣት ያረፈባቸው አሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ሲሆኑ ቡድናቸው ከባህር ዳር ከተማ ጋር ካደረገው ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የድህረ ጨዋታ ቃለመጠይቅ አለመስጠታቸው ሪፖርት የተደረገባቸው በመሆኑ ለፈፀሙት ጥፋት በፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት ብር 3000 እንዲከፍሉ ወስኗል።
በተያየዛ ዜና በተጫዋቾች በኩል ፍሪምፖንግ ሜንሱ ፣ ሪችሞንድ ኦዶንጐ ፣ ፍሬው ጌታሁን እና ክሌመንት ቦዬ በተለያዩ 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ የተመለከቱ ሲሆን ተጫዋቾቹም ለፈፀሙት ጥፋት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት 1500 እንዲከፍሉ ተደርጓል።