የአሰልጣኞች አሰትያየት | አዲስ አበባ ከተማ 1-2 ሲዳማ ቡና

የዕለቱ የመጀመሪያ ከነበረው የአዲስ አበባ ከተማ እና ሲዳማ ቡና መርሐ-ግብር መጠናቀቅ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል።

ጳውሎስ ጌታቸው – አዲስ አበባ ከተማ

ስለጨዋታው

“መጀመሪያም እንዳልኩት ተጫዋቾቼ ላይ ያለ ልክ መጓጓት ነበር በተለይ የመሀል ተከላካዮቻችን ፍፁም አልተረጋጉም የተቆጠረብን ግብ ያንን ያሳያል። እንደ አጠቃላይ አስጠብቀን ለመውጣት የነበረን ግረት ልክ አልነበረም ለዚህም መሸነፋችን ተገቢ ነው።”

ግብ ለማስቆጠር ስለነበራቸው ጥረት

“የሚደረገውን ሁሉ ለማድረግ ሞክረናሌ ነገርግን የዛሬውን ጨዋታ በማሸነፍ አጠቃላይ ያለውን ነገር ዛሬ ላይ ለመቋጨት የነበረው ፍላጎት ከልክ ያለፈ ነበር ስለዚህ ያ ነገር አልተሳካልንም። አሁንም ቢሆን ግን የሚፈጠር ነገር የለም በእርግጠኝነት በሊጉ እንቆያለን።”

በቀጣይ ከጊዮርጊስ ጋር ስለሚጠብቃቸው ጨዋታ

“እኛ የራሳችን እድል በራሳችን ነው የምንወስነው ስለሌላው አያገባንም ትኩረት የምናደርገው የራሳችን ነገር ላይ ነው ምክንያቱን እድሉ እጃችን ላይ እያለ ሌላው ላይ ትኩረት ማድረግ በራሱ ሀጢያት ነው።የራሳችንን ጨዋታ አሸንፈን በሊጉ ለመቆየት እንጥራለን።”

ይህን ጨዋታ መሸነፋቸው ስለሚፈጥርባቸው ተፅዕኖ

“ጠብቀነው ነው ምክንያቱም እነሱ 3ኛ ደረጃ ለማስጠበቅ እኛ ደግሞ ካለንበት ለመውጣት የሚደረጅ ጨዋታ እንደመሆነ ጠንካራ ጨዋታ ይሆናል ብለን ጠብቀን ነበር ፤ ቀጣይም ጠንካራ ጨዋታ ቢገጥመንም እንደ አመጣጡ እንመልሰዋለን።”

ወንድማገኝ ተሾመ – ሲዳማ ቡና

ስለጨዋታው

“የመጀመሪያ አጋማሽ በተወሰነ መልኩ በፈለግነው መንገድ አልሄደልንም ፤ በተጨማሪም ጊት ተጨማሪ ቢጫ ሊያይብን ይችላል የሚል ስጋት ስለነበረብን ማስተካከያ አድርገን ቡድኑን ወደነበረበት መልሰናል በሁለተኛው አጋማሽም ተነጋግረን የምንፈልገውን ነገር ይዘን ወጥተናል።”

ከጨዋታው በፊት ያቀዱትን ስለማሳካታቸው

“አንዳንዴ አስበሀው የመጣኸው ቀመር ካልሰራ ጨዋታው ወደ ሁለተኛው አጋማሽ ማምራቱ አይቀሬ ነው በሁለተኛው አጋማሽ ግን ሁለተኛ እቅዳችን ሰርቶ የምንፈልገውን ይዘን ወጥተናል።”

የተለያዩ ተጫዋቾች ግብ እያስቆጠሩ ስለመሆናቸው

“ቡድናችን ላይ የትኛውም ተጫዋች ግብ ማስቆጠር ይችላል ልምምድ ላይም የምንሰራው ይህን ነው በመሆኑም በአጥቂዎች ላይ ብቻ ጥገኛ አይደለንም።”