በሀዋሳ ከተማ በነገው ዕለት የሚጀመረው የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የዕጣ ማውጣት ስነ-ሥርአት በዛሬው ዕለት ተከናውኗል፡፡
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን አዘጋጅነት በየአመቱ የሚደረገው የክልል ክለቦች ሻምፒዮና ከሰኔ 27 ጀምሮ በሀዋሳ ከተማ መደረግ ይጀምራል፡፡ ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት ክልሎች የውስጥ ውድድራቸውን አድርገው ወደ ውድድሩ የላኳቸውን ክለቦች ለመደልደል ይረዳ ዘንድ አስቀድሞ የሚደረገው የዕጣ ማውጣት ስነ-ሥርአት ዛሬ ከቀትር በኋላ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የመሰብሰቢያ አዳራሽ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የውድድር ዳይሬክተር አቶ ከበደ ወርቁ እና ሌሎች የውድድሩ ኮሚቴዎች እንዲሁም የክለብ አመራሮች እና ተወካዮች በተገኙበት ተከናውኗል፡፡
42 ክለቦችን የሚያሳትፈው የወንዶቹ ውድድር በአስራ አንድ ምድብ የተከፈለ ድልድል የተከናወነበት ሲሆን በነገው ዕለት አመሻሹን ደግሞ የሴት ክለቦች የዕጣ ማውጣት መርሐ-ግብር እንደሚደረግ የውድድሩ ኮሚቴ ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቀዋል ፡፡
ነገ በሦስት ሜዳዎች በሚደረጉ አስራ ሁለት ጨዋታዎች የወንዶቹ ውድድር የሚጀምር ሲሆን የምደብ ድልድሉም ይሄን ይመስላል፡፡
ምድብ 1 ☞ አቦከር ወረዳ ፣ ዳሌ ወረዳ ፣ ኦዳ ሁሌ ሆስፒታል ፣ 06 ሕብረት
ምደብ 2 ☞ አለታ ወንዶ ከተማ ፣ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፣ ገንደ ሸቤል
ምድብ 3 ☞ አኳ ድሬ ፣ ሳሪስ አዲስ ሰፈር ፣ ዶሬ ባፋኖ ወረዳ ፣ ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ
ምድብ 4 ☞ ቤንሻንጉል ፓሊስ ፣ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፣ የኛ አዲስ ከቴ ፣ ቅበት ወረዳ
ምድብ 5 ☞ ዶዮ ገና ከተማ ፣ ኡዱሉ ወረዳ ፣ በደሌ ከተማ ፣ ሞጣ ከተማ
ምድብ 6 ☞ ሀረር ዩናይትድ ፣ ግምጃ ቤት ከተማ ፣ ቤቴል ድሪመር
ምድብ 7 ☞ ሀዋሳ ተስፋ ፣ ዳባት ከተማ ፣ ሀላባ ሸገር ፣ ሠመራ ሎጊያ
ምድብ 8 ☞ ሻኪሶ ከተማ ፣ ቦሌ ገርጂ ፣ ኛንጋቶም ወረዳ ፣ ገንደ ተስፋ
ምድብ 9 ☞ ሶከሩ ከተማ ፣ ሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ፣ ድሬ ካባ ፣ አዴት ከተማ
ምድብ 10 ☞ ዱብቲ ወረዳ ፣ ሀርቡ ከተማ ፣ ሐረር ፖሊስ ፣ 18ቱ ኮከቦች
ምድብ 11 ☞ ቦርቻ ወረዳ ፣ አባዲር ወረዳ ፣ ሆርሞድ