ለዋልያዎቹ ጥሪ ተደርጓል

ከደቡብ ሱዳን ጋር የቻን ማጣሪያ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስቡን ይፋ አድርጓል።

በአልጄሪያ አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የቻን የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ ሱዳን ጋር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ እንደሚጠብቀው ይታወቃል። ሐምሌ 15 እና 24 ለሚደረጉት እነዚህ ሁለት ጨዋታዎች የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጨዋቾች ጥሪ ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል። በተጨማሪም ተጫዋቾቹ ሐምሌ 04 በፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ ተጠቁሟል።

ግብ ጠባቂዎች

ፋሲል ገብረሚካኤል (ባህር ዳር ከተማ)
በረከት አማረ (ኢትዮጵያ ቡና)
አላዛር ማርቆስ (ጅማ አባ ጅፋር)

ተከላካዮች

ሱሌይማን ሀሚድ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ሄኖክ አዱኛ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ምኞት ደበበ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ያሬድ ባየህ (ፋሲል ከነማ)
ሚሊዮን ሰለሞን (አዳማ ከተማ)
አስራት ቱንጃ (ኢትዮጵያ ቡና)
ረመዳን የሱፍ (ወልቂጤ ከነማ)
ጊት ጋትኩት (ሲዳማ ቡና)

አማካዮች

ጋቶች ፓኖም (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ከነዓን ማርክነህ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ)
በዛብህ መለዮ (ፋሲል ከነማ)
በረከት ደስታ (ፋሲል ከነማ)
አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና)
መስዑድ መሐመድ (ጅማ አባ ጅፋር)

አጥቂዎች

ቸርነት ጉግሳ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
አማኑኤል ገብረሚካኤል (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ዳዋ ሆቴሳ (አዳማ ከተማ)
ብሩክ በየነ (ሀዋሳ ከነማ)
ይገዙ ቦጋለ (ሲዳማ ቡና)

ያጋሩ