ዋልያዎቹ የሚዘጋጁባት ከተማ ታውቃለች

ለቻን አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታውን ከደቡብ ሱዳን ጋር የሚያደርገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን የሚያደርግበት ቦታ ታውቋል።

በአልጄሪያ አስተናጋጅነት 2023 ጥር ወር ላይ በሚካሄደውን የአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ቅድመ ማጣርያ ጨዋታውን ለማድረግ ከደቡብ ሱዳን ጋር የተመደበው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቅርቡ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ማስተላለፉ ይታወቃል።

ብሔራዊ ቡድናችን ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ቅደመ ዝግጅቱን እንደሚያደርግ የተገለፀ ቢሆንም በየትኛው ከተማ እንደሚያደርግ የተባለ ነገር አልነበረም ። ሶከር ኢትዮጵያ እንዳገኘቸው መረጃ ከሆነ ብሔራዊ ቡድኑ በአዳማ ከተማ ዝግጅቱን እንደሚያደርግ ታውቋል። የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ እና ረዳታቸው አሰልጣኝ አስራት አባተ ለሥልጠና በሀገረ አሜሪካ የሚገኙ ሲሆን ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ ሱዳን አቻው ጋር ሐምሌ15 እና ሐምሌ 24 ቀን በታንዛንያ ከተማ ጨዋታውን እንደሚያደርግ ይታወቃል።

ያጋሩ