ረመዳን የሱፍ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች ሆኗል

ከደቂቃዎች በፊት ከጫፍ መድረሱን ዘግበን የነበረው የረመዳን የሱፍ ዝውውር መጠናቀቁ ይፋ ተደርጓል።

የፕሪምየር ሊጉ ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ ራሱን ጠንካራ ተፎካካሪ ለማድረግ ቡድኑን ማጠናከር ጀምሯል፡፡ ከደቂቃዎች በፊት ወደ ክለቡ ይቀላቀላል ብለናችው የነበረው ወጣቱ የግራ መስመር ተከላካይ በይፋ ክለቡን ተቀላቅሏል፡፡

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተገኘው ይህ ተጫዋች በስሐል ሽረ እና ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ በወልቂጤ ከተማ ቆይታን ካደረገ በኋላ ፈረሰኞቹን በሁለት ዓመት ውል ተቀላቅሏል፡፡

ያጋሩ