ቅዱስ ጊዮርጊስ ባለ ድሎቹን ሊሸልም ነው

የ2014 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባለ ድል የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ለቡድን አባላቱ ሽልማት ሊያበረክት ነው።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በአዲስ መልክ 1990 ላይ መከናወን ከጀመረ አንስቶ ለአስራ አምስተኛ ጊዜ ዋንጫውን ዘንድሮ በማንሳት ታላቅነቱን ያሳየው ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2014 የውድድር ዘመን ሻምፒዮን ያደረጉትን የቡድኑን አባላት በነገው ዕለት ከምሽቱ 12:30 ጀምሮ በጽሕፈት ቤቱ ባዘጋጀው መርሐግብር ሊሸልም ነው።

ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በሚታደሙበት በዚህ መድረክ ላይ ለቡድኑ አባለት ከሚበረከተው የገንዘብም ሆነ ሌሎች ሽልማቶች በተጨማሪ የክለቡን የፋይናስ አቅም ሊያሳድጉ ይችላል ተብሎ ከታመነባቸው ተቋማት ጋር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ይፈፅማል ተብሎ ይጠበቃል።

ያጋሩ