በክልል ክለቦች ሻምፒዮና በጥሎ ማለፍ የሚፋለሙ ክለቦች ተለይተው ታወቁ

በአርባ ሁለት ክለቦች መካከል እየተደረገ የሰነበተው የክልል ክለቦች ሻምፒዮና ከምድብ ያለፉ ክለቦች ተለይተው ታውቀውበታል።

በሀዋሳ ከተማ ከሰኔ 27 ጀምሮ በተለያዩ ሜዳዎች እየተደረገ የሰነበተው የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ከየምድቦቹ ከተደረጉ ጨዋታዎች ወደ ጥሎ ማለፉ ውስጥ የገቡ ቡድኖች ሙሉ በሙሉ በዛሬው ዕለት ታውቀዋል፡፡ በዚህም መሠረት ከአስራ አንዱ ምድቦች በደሌ ከተማ ፣ ሆሞሻ ሸንጋ ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ ቅበት ከተማ ፣ ኦሮሚያ ፓሊስ ኮልጅ ፣ ቤተል ድሪመር ፣ ሀላባ ሸገር ፣ ቤቴል ድሪመር ፣ ሆርሙድ ፣ ሞጣ ከተማ ፣ አለታ ወንዶ ከተማ ፣ ሻኪሶ ከተማ ፣ ዶሬ ባፋኖ ፣ አዴት ከተማ ፣ ዳባት ከተማ ፣ ሀርቡ ከተማ ፣ ዳባት ከተማ እና ሶከሩ ከተማ ያረጋገጡ ክለቦች ናቸው፡፡

በነገው ዕለት ድልድል ወጥቶ ከነገ በስቲያ ረቡዕ ጀምሮ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ከተደረጉ በኋላ ወደ 2015 የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የሚያልፉ ክለቦች የሚለዩ ይሆናል፡፡

ያጋሩ