ዱሬሳ ሹቢሳ የጣናው ሞገዶቹን ተቀላቅሏል

ባህር ዳር ከተማ ፈጣኑን የመስመር አጥቂ ዱሬሳ ሹቢሳን የግሉ አድርጓል።

በትናንትናው ዕለት በይፋ የዝውውር ገበያውን የተቀላቀለው ባህር ዳር ከተማ ያሬድ ባየህን ማስፈረሙን እና ከቻርለስ ሪባቡ ጋር በቃል ደረጃ መስማማቱን ዘገበን ነበር። አሁን ባገኘነው መረጃ ደግሞ ፈጣኑን የመስመር አጥቂ ዱሬሳ ሹቢሳን በሁለት ዓመት ውል አስፈርመዋል።

ከአዳማ ወጣት ቡድን ተገኝቶ በአርሲ ነገሌ የተሰረዘውን ዓመት ቆይታ ካደረገ በኋላ
2013 ላይ ሰበታ ከተማን ተቀላቅሎ የነበረው ዱሬሳ የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመትም በክለቡ ግልጋሎት ሲሰጥ የቆየ ሲሆን አሁን ዳግም ከቀድሞ አሠልጣኙ አብርሃም መብራቱ ጋር ለመስራት ባህር ዳርን ምርጫው አድርጓል።

ያጋሩ