ሙሉቀን አዲሱ እና ሲዳማ ቡና ተስማሙ

ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር በግሉ ጥሩ የውድድር ዓመት ያሳለፈው አማካይ ለሲዳማ ቡና ለመጫወት በቃል ደረጃ ተስማምቷል፡፡

በ2014 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በደረጃ ሰንጠረዡ ሦስተኛ ላይ ተቀምጠው ያጠናቀቁት ሲዳማ ቡናዎች በትላንትናው ዕለት ወንድማገኝ ተሾመን በዋና አሰልጣኝነት መሾማቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ወደ ዝውውር ገበያው በመግባት አማካይ ለማስፈረም ቅድመ ስምምነት ፈፅመዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር ዓመቱን ያሳለፈው የቀድሞው የአርሲ ነገሌ እና ገላን ከተማ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው ሙሉቀን አዲሱ ለሲዳማ ቡና ለቀጣዮቹ ሁለት የውድድር ዓመታት ለመጫወት በቃል ደረጃ ቅድመ ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡ ክለቡም ዝውውሩን ዛሬ ከሰዓት አልያም በነገው ዕለት ረፋድ ላይ ያጠናቅቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ያጋሩ