የካፍ ፕሬዝዳንት አዲስ አበባ ገብተዋል

የካፍ ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሙትሴፔ ለአንድ ቀን የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ መግባታቸው ታውቋል።

የአፍሪካ እግር ኳስ ማኅበር የበላይ የሆነውን ተቋም በፕሬዝዳንትነት የሚመሩት ፓትሪስ ሙትሴፔ ረፋድ ላይ አዲስ አበባ መግባታቸው ታውቋል። ፕሬዝዳንቱ ወደ ኢትዮጵያ የመጡበት ምክንያት ባይታወቅም ካፍ በድረ-ገፁ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ከኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ከኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ እና ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ እንዲሁም በእግር ኳሱ እና ቢዝነስ ዙሪያ ካሉ አካላት ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ተጠቁሟል።

ያጋሩ