ሲዳማ ቡና የሁለት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቀቀ

ሊጉን በሦስተኝነት ያገባደደው ሲዳማ ቡና ሁለት አማካዮችን አስፈርሟል።

በአሰልጣኝ ወንድማገኝ ተሾመ የሚመሩት ሲዳማ ቡናዎች በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ ጥሩ እንቅስቃሴ ያደረጉ ሁለት ተጫዋቾችን በቡድናቸው ማካተት ችለዋል።

በረፋዱ ዘገባችን የቀድሞውን የአርሲ ነገሌ እና ገላን ከተማ ተጫዋች የነበረው እና ዘንድሮ በአዲስ አበባ ከተማ የተመለከትነው አማካዩ ሙሉቀን አዲሱ ወደ ሲዳማ ቡና ለማምራት ስለመስማማቱ ገልፀን የነበረ ሲሆን ተጫዋቹ ከደቂቃዎች በፊት በይፋ ለክለቡ የሁለት ዓመት ውልን ፈርሟል፡፡

እንዳለ ከበደም ከሰባት ዓመታት በኋላ የቀድሞው ክለቡን ተቀላቅሏል፡፡ ከአርባምንጭ ከተማ ከተገኘ በኋላ ለሲዳማ ቡና ፣ መቐለ 70 እንደርታ ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ዘንድሮ ደግሞ በመዲናይቱ ክለብ አዲስ አበባ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ ወደ ቀድሞው ክለቡ በማቅናት አብሮት ከተጫወተው ወንድማገኝ ተሾመ ጋር ለመስራት የሁለት ዓመት ውል ፈርሟል፡፡

ያጋሩ