ፈረሰኞቹ ተጨማሪ ተጫዋች አስፈርመዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ የዳዊት ተፈራን ዝውውር ማገባደዱን ይፋ አድርጓል።

የረመዳን የሱፍ እና ቢኒያም በላይን ዝውውር ከሰሞኑ ያገባደደው ቅዱስ ጊዮርጊስ አሁንም በዝውውሩ ተሳትፎ የአጥቂ አማካይ የግሉ ማድረጉን ይፋ አድርጓል። ቡድኑን የተቀላቀለው ተጫዋችም ዳዊት ተፈራ ነው።

ከመከላከያ ታዳጊ ቡድን ከወጣ በኋላ ከ2007 እስከ 2010 ድረስ በጅማ አባ ቡና ሲጫወት የነበረው አማካዩ ከ2011 ጀምሮ ያለፉትን አራት ዓመታት በሲዳማ ቡና ቆይታን አድርጎ ነበር። አሁን ደግሞ የእግር ኳስ ህይወቱን በቅዱስ ጊዮርጊስ ለመቀጠል የ2 ዓመት ውል ፈርሟል።

ያጋሩ