የእግርኳሱ የበላይ አካል በሙጂብ ቃሲም ጉዳይ ዙሪያ ውሳኔ ማስተላለፉን ተጫዋቹ ለዝግጅት ክፍላችን ገልጿል።
ሙጂብ ቃሲም በዚህ ዓመት መጀመርያ የአልጄሪያውን ክለብ ጄኤስ ካቢሌ ተቀላቅሎ የቅድመ ውድድር ዝግጅትም ሆነ በተወሰኑ የሊጉ ጨዋታዎች ላይ ተሳትፎ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ደሞዝ እና አንዳንድ ጥቅማጥቅሞች ወቅቱን ጠብቀው ባለመከፈላቸው ምክንያት የፊፋን የዝውውር ደንብ በተከተለ መልኩ ውሉን አቋርጦ ወደ ዐፄዎቹ ቤት መመለሱ ይታወቃል።
ወደ ቀድሞ ክለቡ ሀዋሳ የመለሰውን ዝውውር ከትናንት በስትያ ያገባደደው ሙጂብ በውሉ መሠረት ያልተከፈለውን ክፍያ በጠበቃው ሳይፐርስ እና በኢትዮጵያዊው ወኪል ቢንያም ሚዴቅሳ አማካኝነት ወደ ፊፋ ክስ አቅርቦ ነበር። ፊፋም ጉዳዮን ከመረመረ በኋላ ሙጂብ ቃሲም በውሉ መሰረት ሙሉ ጥቅሙ ተጠብቆ ያልተከፈለው ክፍያ እንዲከፈል ውሳኔ ማሳለፉ ተጫዋቹ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል።