አርባምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ተጫዋቹን አግኝቷል

ከአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ጋር በቀጣዮቹ ዓመታትም የሚዘልቀው አርባምንጭ ከተማ የመሀል ተከላካይ አስፈርሟል፡፡

ወደ ፕሪምየር ሊጉ ካደገ በኋላ ለከርሞው በሊጉ መቆየቱን ያረጋገጠው አርባምንጭ ከተማ ከአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ጋር ለቀጣዮቹ አንድ ዓመታት እንደሚቀጥል ቀደም ባለው ዘገባችን የጠቆምናችሁ ሲሆን ከሰዓታት በፊት ደግሞ ወደ ዝውውር በመግባት አዩብ በቀታን የግሉ አድርጓል፡፡

የቀድሞው የሀድያ ሆሳዕና የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች በዘንድሮው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ከከፍተኛ ሊጉ ክለብ ሀላባ ከተማ በውሰት ወደ አዲስ አበባ ከተማ በማምራት ያለፉትን ስድስት ወራት ማሳለፍ ከቻለ በኋላ ለቀጣዩ አንድ ዓመት ለአርባምንጭ ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል፡፡

ያጋሩ