ሀብታሙ ታደሠ ባህር ዳር ከተማን ተቀላቅሏል

በአሠልጣኝ አብርሃም መብራቱ የሚመሩት ባህር ዳር ከተማዎች አራተኛ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል።

እስከ ዛሬ ፍፁም ጥላሁን ፣ ዱሬሳ ሹቢሳ እና ያሬድ ባየህን ዝውውር ያጠናቀቁት ባህር ዳር ከተማዎች ከደቂቃዎች በፊት ሀብታሙ ታደሰን የግላቸው ማድረጋቸው ታውቋል።

በወልቂጤ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ከተጫወተ በኋላ ወደ ሀዲያ ሆሳዕና በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ያመራው ሀብታሙ በክለቡ ቀሪ የአንድ ዓመት ውል የነበረው ቢሆንም በስምምነት በማቋረጥ ወደ ጣና ሞገዶቹ አምርቷል። በአጥቂ ስፍራ ላይ ከፍፁም ጥላሁን እና ዱሬሳ ሹቢሳ በመቀጠል ሦስተኛው ፈራሚ የሆነው ሀብታሙ በቦታው ጥሩ አማራጭ እንደሚፈጥር ይጠበቃል።

ያጋሩ