ብርሀኑ አሻሞ የቀድሞው ክለቡን ተቀላቀለ

ሀዋሳ ከተማ የአማካይ ክፍሉን ያጠናከረበትን ዝውውር አጠናቋል።

በዝውውር ገበያው በንቃት ተሳትፎን እያደረገ የሚገኘው ሀዋሳ ከተማ የቀድሞው ተጫዋቹን አስፈርሟል፡፡ ከበረከት ሳሙኤል ፣ እዮብ ዓለማየሁ ፣ ሙጂብ ቃሲም ፣ አዲሱ አቱላ እና ሰዒድ ሀሰን በመቀጠል ስድስተኛ የሆነው ተጫዋች የተከላካይ አማካዩ ብርሀኑ አሻሞ ሲሆን ከታላቅ ወንድሙ ኤፍሬም አሻሞ ጋር በአንድ መለያ ለመጫወት ሀዋሳን አመሻሽ ተቀላቅሏል፡፡

በእግርኳስ ህይወቱ ጅማሮ ከሀዋሳ ከተማ ወጣት ቡድን እስከ ዋናው ያለገለገለው እና በደደቢት ፣ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ እና ያለፉት ሦስት ዓመታት በሲዳማ ቡና ያሳለፈው ተጫዋቹ በልጅነቱ ግልጋሎት የሰጠበትን ክለብ ዳግም ለማገልገል በሁለት ዓመት ውል ኃይቆቹን ተቀላቅሏል፡፡

ያጋሩ