ምንይሉ ወንድሙ ወደ ቀድሞ ቤቱ ተመልሷል

የሦስት ተጫዋቾችን ዝውውር ያገባደደው እና ከአንድ ተጨማሪ ተጫዋች ጋር ቅድመ ስምምነት የፈፀመው መከላከያ አጥቂ የግሉ አድርጓል።

በዛሬው ዕለት በረከት ደስታ፣ ዳግም ተፈራ እና ሳሙኤል ሳሊሶን በሁለት ዓመት ውል ያስፈረሙት መከላከያዎች ከከነዓን ማርክነህ ጋርም በሁሉም ቅድመ ሁኔታዎች ጋር መስማማታቸውን አስነብበናችሁ ነበር። አሁን ባገኘነው መረጃ ደግሞ የውድድር ዓመቱን በወላይታ ድቻ ያሳለፈው ምንይሉ ወንድሙ የጦሩ ተጨማሪ ተጫዋች ሆኗል።

በመከላከያ ለዓመታት ከዚህ ቀደም መጫወት የቻለው ምንይሉ ከዛም የእግር ኳስ ህይወቱን ወደ መቐለ 70 እንደርታ እና ወደ ባህር ዳር በመጓዝ የቀጠለ ሲሆን ዓምና ደግሞ በአሠልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም የሚመራውን ወላይታ ድቻ ተቀላቅሎ ግልጋሎት ሲሰጥ ቆይቶ ነበር። አሁን ደግሞ ዳግም የቀደመ ክለቡን ተቀላቅሎ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል።

ያጋሩ