ድሬዳዋ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ሊሾም ነው

ከአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ጋር በስምምነት የተለያየው ድሬዳዋ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ማግኘቱ ተሰምቷል።

ለ2015 የውድድር ዘመን በተሻለ አቀራርብ ለመምጣት የተለያዩ ውሳኔዎችን እያሳለፈ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ ያለፉትን 15 ሳምንት ከቡድኑ ጋር ቆይታ ካደረጉት ከአሰልጣኝ ሳምሶም አየለ ጋር በስምምነት መለያየቱን ከደቂቃዎች በፊት ዘግበን ነበር። በምትካቸውም የክለቡ ስራ አመራር ቦርድ ባደረገው ውይይት አሰልጣኝ ዮርዳኖስ አባይን ለአንድ ዓመት ለመሾም መወሰኑን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በኢትዮጵያ እግርኳስ ጎልተው ከወጡ ከዋክብቶች መካከል አንዱ የሆነው ዮርዳኖስ ጫማውን ከሰቀለ በኋላ ወደ አሰልጣኝነቱ በመግባት በናሽናል ሲሚንት እና ድሬዳዋ ፖሊስ የአሰልጣኝነት ህይወትን የጀመረ ሲሆን ያለፉትን ሁለት አመታት በመከላከያ በምክትል አሰልጣኝነት ሲሰራ መቆየቱ አይዘነጋም።

ያጋሩ