መከላከያ የሁለት ወሳኝ ተጫዋቾችን ውል አድሷል

በትናንትናው ዕለት በይፋ በዝውውሩ መሳተፍ የጀመረው መከላከያ የሁለት ነባር ተጫዋቾቹን ውል አድሷል።

በረከት ደስታ፣ ሳሙኤል ሳሊሶ፣ ዳግም ተፈራ እና ምንይሉ ወንድሙን በይፋ አስፈርሞ ከከነዓን ማርክነህን ጋር ቅድመ ስምምነት የፈፀመው መከላከያ በዛሬው ዕለት የነባር ተጫዋቾቹን ውል ማደስ ጀምሯል። ውሉን ለተጨማሪ ዓመት ያራዘመው የመጀመሪያው ተጫዋች ፋሲል ከነማ እና ባህር ዳር ከተማን ጨምሮ በበርካታ ክለቦች ሲፈለግ የነበረው የመስመር ተከላካዩ ዳዊት ማሞ ነው። የቀድሞ የአዲስ አበባ ከተማ ተጫዋች የነበረው ዳዊት 2010 ወደ መከላከያ በማምራት በከፍተኛ ሊግ እና ፕሪምየር ሊግ ቡድኑን ሲያገለግል ነበር።

ሁለተኛው ተጫዋች ደግሞ አምበሉ አሌክስ ተሰማ ነው። መቐለ 70 እንደርታን ወደ ሊጉን እንዲያድግ ትልቅ ሚና ተጫውቶ የነበረው አሌክስ የሊጉንም ዋንጫ ከክለቡ ጋር ማንሳቱ አይዘነጋም። በመከላከያም ጥሩ ቆይታን ያደረገ ሲሆን እንደ ዳዊት ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል።

ያጋሩ