ሀዋሳ ከተማ ተከላካይ አስፈርሟል

ሀዋሳ ከተማ የሰባተኛ ተጫዋች ዝውውር አጠናቋል።

በአሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ መሪነት በተጫዋቾች የዝውውር ገበያ ላይ የነቃ ተሳትፎን እያደረገ የሚገኘው ሀዋሳ ከተማ ከእዮብ አለማየሁ ፣ በረከት ሳሙኤል ፣ ሙጂብ ቃሲም ፣ ሰይድ ሀሰን ፣ አዲሱ አቱላ እና ብርሃኑ አሻሞ ቀጥሎ ሰባተኛ ተጫዋቹ ሰለሞን ወዴሳን ለሁለት ዓመት አድርጓል፡፡

እግርኳስን በሀዋሳ ከተማ ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድኖች እና በዋናውም ቡድን ውስጥ ተጫውቶ ያሳለፈው በተከላካይ አማካይ እና በተከላካይነት የሚያገለግለው ተጫዋቹ በኢትዮጵያ መድን እንዲሁም ደግሞ ያለፉትን ሦስት ዓመታት በባህር ዳር ከተማ ከቆየ በኋላ ወደ ልጅነት ክለቡ የሚመልሰውን ዝውውር ከሰዓታት በፊት ፈፅሟል፡፡

ያጋሩ