ወላይታ ድቻ የመጀመሪያ ተጫዋቹን አስፈረመ

የአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን ውል ያራዘመው ወላይታ ድቻ የመጀመሪያ ተጫዋቹን አግኝቷል፡፡
የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በደረጃ ሰንጠረዡ አምስተኛ ላይ ተቀምጦ ማጠናቀቅ የቻለው ወላይታ ድቻ ከትናንት በስትያ የአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን እና የአማካዩ መሳይ ኒኮልን ውል ለተጨማሪ ዓመት ማራዘሙ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ አዲስ የግራ መስመር ተከላካይን የግሉ አድርጓል፡፡

ሳሙኤል ተስፋዬ የክለቡ የመጀመሪያው ፈራሚ ሆኗል፡፡ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ከተገኘ በኋላ በባህርዳር ከተማ እንዲሁም የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ ያሳለፈው ተጫዋቹ ቀጣይ መዳረጋቸውን የጦና ንቦቹ ቤት አድርጓል፡፡

ያጋሩ