ኢትዮ ኤሌክትሪክ ግብ ጠባቂ አስፈርሟል

አዲስ አዳጊው ክለብ ኢትዮ ኤሌክትሪክ የመጀመርያው ፈራሚ ግብ ጠባቂ ሆኗል።

በአሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና የሚመራው ኢትዮ ኤሌትሪክ ራሱን ወደ ዝውውር በማስገባት የመጀመርያው ፈራሚ ወጣቱ ግብ ጠባቂ መሆኑ ተረጋግጧል። ለአንድ ዓመት በኢትዮ ኤሌክትሪክ ቤት የሚያቆየውን ውል የፈፀመው ግብ ጠባቂው ሰለሞን ደምሴ ሲሆን የተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ጨምሮ አብዛኛውን የእግርኳስ ህይወቱን በሰበታ ከተማ ካሳለፈ በኋላ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለተኛው ክለቡ ሆኗል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ቡድኑን ለማጠናከር በዚህ ሳምንት በስፋት ወደ ዝውውሩ በመግባት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ያስፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ያጋሩ