ባህርዳር ከተማ አማካይ አስፈረመ

የአሰልጣኝ አብርሃም መብራቱው ባህርዳር ከተማ ያብስራ ተስፋዬን የግሉ አድርጓል፡፡

ለቀጣዩ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ተጠናክሮ ለመቅረብ ቡድናቸውን እያጠናከሩ ካሉ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ባህርዳር ከተማ አማካዩ ያብስራ ተስፋዬን አስፈርሟል፡፡

የቀድሞው የደደቢት የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ያለፉትን አራት የውድድር ዘመናት በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ቆይታ ያደረገ ሲሆን በትላንትናው ዕለት ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እየቀረው ከክለቡ ጋር ከተለያየ በኋላ በዛሬው ዕለት በይፋ የጣና ሞገደኞቹን በሁለት ዓመት ውል ዛሬ ተቀላቅሏል፡፡

ያጋሩ