ኢትዮ ኤሌክትሪክ የአንዳርጋቸው ይላቅን ውል አድሷል

ከከፍተኛ ሊጉ ዳግም ወደ ፕሪምየር ሊጉ የተመለሰው ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ የተከላካዩን ውል ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል፡፡

የአሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተናው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የነባር ተጫዋቾች ውል በማደስ እንዲሁም የአዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር በመፈፀም ላይ የሚገኝ ሲሆን አሁን ደግሞ ክለቡ ከከፍተኛ ሊጉ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲመለስ በቡድኑ ውስጥ የነበረውን የመስመር ተከላካይ ውል አድሷል፡፡

የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ አዳማ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና ተከላካይ አንዳርጋቸው ይላቅ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በኤሌክትሪክ ያሳለፈ ሲሆን በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ላይ ከክለቡ ጋር ተጨማሪ ሦስተኛ ዓመትን ለመቆየት ውሉን አድሷል፡፡

ያጋሩ