ሀድያ ሆሳዕና የመስመር አጥቂ አስፈርሟል

ሁለት የውድድር ዓመታትን በመከላከያ ያሳለፈው የመሰመር አጥቂ ሀዲያ ሆሳዕናን ተቀላቅሏል።

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለቀጣዩ ዓመት ተጠናክሮ ለመቅረብ ከሰሞኑ ወደ ዝውውር ገበያው በመግባት ተከላካዩ ዳግም ንጉሴ እና አማካዩ ቤዛ መድኅንን የግሉ ማድረግ የቻለው ሀድያ ሆሳዕና ሦስተኛ አዲስ ፈራሚው የመስመር አጥቂው ሠመረ ሀፍታይ ሆኗል፡፡

የቀድሞው የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ተጫዋች ከ2013 ጀምሮ በከፍተኛ ሊጉ ከመከላከያ ጋር ወደ ፕሪምየር ሊጉ በማደግ እስከ ተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በጦሩ ቤት አሳልፏል። ሠመረ ለቀጣዩ አንድ ዓመት ደግሞ ለነብሮቹ ለመጫወት በዛሬው ዕለት ፊርማውን አኑሯል፡፡

ያጋሩ