ኃይሌ ገብረተንሳይ ማረፊያው ታውቋል

ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ቀሪ የሦስት ዓመት ቆይታ እያለው በስምምነት የተለያየው ኃይሌ ገብረትንሳይ አዲስ አዳጊውን ክለብ ተቀላቅሏል።

ለመጪው የውድድር ዘመን በቡድኑ ውስጥ ጥሩ ግልጋሎት የነበራቸውን ተጫዋቾቹን ውል እያራዘመ የሚገኘው እና የጥቂት ተጫዋቾችን ዝውውር ያጠናቀቀው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የመስመር ተከላካዩ ኃይሌ ገብረትንሳይን አስፈርሟል።

ከኢትዮጵያ ቡና የታችኛው ቡድን በመገኘት ከ2010 ጀምሮ ወደ ዋናው ቡድን በማደግ ያለፉትን አራት ዓመታት ሲያገለግል የቆየው የቀኝ መስመር ተከላካዮ ኃይሌ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ለአንድ ዓመት ለመጫወት መስማማቱን አውቀናል።

በአንድ ዓመት ውል ብቻ ተጫዋቾችን እያስፈረመ የሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በቀጣይ ተጨማሪ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ይቀላቅላል ተብሎ ይጠበቃል።

ያጋሩ