ኢትዮ ኤሌክትሪክ ግብ ጠባቂ አስፈርሟል

በዝውውሩ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለተኛ ግብጠባቂ አስፈርሟል።

ከአራት ዓመት በኋላ ወደ ሊጉ ዳግም የተመለሰው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከረፋድ ጀምሮ የተለያዩ ተጫዋቾችን በማስፈረም እና ውል በማደዝ ላይ ይገኛል። አሁን ደግሞ የግብ ዘቡን ፍቅሩ ወዴሳን ማስፈረሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

አብዛኛውን የእግርኳስ ህይወቱን በሲዳማ ቡና ያሳለፈው ፍቅሩ ወዴሳ ለኢትዮ ኤሌክትሪክ ለአንድ አመት ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል። አስቀድመው የግብ ጠባቂው ዘሪሁን ታደለን ውል ካራዘሙ በኋላ የሰበታውን ግብ ጠባቂ ሰለሞን ደምሴን ያስፈረሙት ኤሌክትሪኮች ፍቅሩን በቦታው ሌላ አማራጭ አድርገው ወደ ስብስባቸው ቀላቅለዋል።

ያጋሩ