ኢትዮ ኤሌክትሪክ ስድስተኛ ፈራሚውን አግኝቷል

በተለያዩ ክለቦች ተጫውቶ ያሳለፈው ተከላካይ ተስፋዬ በቀለ ወደ ኢትዮ ኤሌክትሪክ አምርቷል።

ግብ ጠባቂዎቹን ፍቅሩ ወዴሳ እና ሰለሞን ደምሴን እንዲሁም ተከላካዮቹ ኃይሌ ገብረትንሳይ፣ ጌቱ ኃይለማርያምን እና ታፈሰ ሰርካን ወደ ስብስባቸው የቀላቀሉት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ስድስተኛ ፈራሚያቸው ተከላካዩ ተስፋዬ በቀለ ሆኗል።

ከኢትዮጵያ ቡና እና ከመቐሌ 70 እንድርታ ጋር የሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻለው ተስፋዬ በመከላከያ፣ በአዳማ ከተማ፣ በሀድያ ሆሳዕና እና በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሲዳማ ቡና ያሳለፈ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ከኤሌክትሪክ ጋር ለአንድ ዓመት ለመጫወት ተስማምቷል። በተለያዩ ቦታዎች የመጫወት ልምድ ያለው ተስፋዬ ለቡድኑ አማራጭ ያሰፋል ተብሎ ይጠበቃል።

አሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና በቀሩት ቀናት የአምስት ተጫዋቾችን ዝውውር እንደሚያጠናቅቁ ሰምተናል።

ያጋሩ