የአቤል ማሞ ማረፊያው ታውቋል

ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያለፉትን ሁለት ዓመታት ቆይታ ያደረገው የግብ ዘቡ አቤል ማሞ ወደ ሌላኛው የሊጉ ክለብ አምርቷል።

በ2014 ዳግም ወደ ሊጉ በመመለስ መልካም የውድድር ዘመን ያሳለፈው አርባምንጭ ከተማ ለከርሞው ውድድር እራሱን ለማጠናከር በዝውውሩ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል። የነባር ተጫዋቾቹን ውል ከማራዘም ባለፈ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ እየቀላቀለ ሲገኝ አሁን ደግሞ ግብ ጠባቂውን አቤል ማሞን ማስፈረሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

በሙገር ሲሚንቶ፣ በመከላከያ እና ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ያሳለፈው አቤል ማሞ ለአርባምንጭ ከተማ ለአንድ ዓመታት ለመጫወት መስማማቱን አውቀናል።

ያጋሩ