ወላይታ ድቻ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን የሚጀምርበት ቀን ታውቋል

በአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም መሪነት በቀጣዩ የውድድር ዘመንም የሚዘልቀው ወላይታ ድቻ በነሀሴ ወር መጀመሪያ ዝግጅቱን ይጀምራል፡፡

ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ካደገበት 2006 ጀምሮ ጠንካራ ከሚባሉ ክለቦች ተርታ መሰለፍ የቻለው ወላይታ ድቻ ለ2015 የውድድር ዘመን የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን መቼ እንደሚጀምር ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቋል፡፡

ክለቡ የአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያምን ውል አስቀድሞ ካራዘመ በኋላ በሀይሉ ተሻገር እና ሳሙኤል ተስፋዬን በአዲስ መልክ አስፈርሞ ውላቸው የተጠናቀቀውን ደጉ ደበበ ፣ ንጋቱ ገብረስላሴ ፣ መሳይ ኒኮል ፣ አበባየው ሀጂሶ እና ቢኒያም ፍቅሬን ውል ያደሰ ሲሆን የቅድመ ውድድር ዝግጅቱንም በመቀመጫ ከተማው ሶዶ ነሀሴ 5 ለመጀመር ቀን እንደቆረጠ የዝግጅት ክፍላችን ለማወቅ ችላለች።

ቡድኑ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ሊጉን በአምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ መፈፀሙ ይታወሳል፡፡