ለቻን ማጣርያ 23 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገላቸው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርገው የቻን ማጣርያ የደርሶ መልስ ጨዋታ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ መደረጉን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

በነሐሴ የመጨረሻ ሳምንት እንደሚካሄዱ በሚጠበቀው የመጨረሻ ዙር ማጣርያ ላይ ኢትዮጵያ ሩዋንዳን የምትገጥም ሲሆን ለዚህ ዝግጅት እንዲረዳም አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል። ነሐሴ 4 ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ የቀረበላቸው ተጫዋቾች ዝርዝር ከባለፈው የማጣርያ ጨዋታ ለውጥ እንዳልተደረገበትም ታውቋል።

ግብ ጠባቂዎች : ፋሲል ገ/ሚካኤል (ባህር ዳር ከተማ) ፣ በረከት አማረ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ አላዛር ማርቆስ (ሀዋሳ ከተማ)

ተከላካዮች : ሱሌማን ሀሚድ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ሄኖክ አዱኛ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ጊት ጋትኩት (ሲዳማ ቡና) ፣ ያሬድ ባየህ (ባህር ዳር ከተማ) ፣ ሚሊዮን ሰለሞን (አዳማ ከተማ) ፣ ምኞት ደበበ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ አስራት ቱንጆ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ረመዳን የሱፍ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

አማካዮች : አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ ጋቶች ፓኖም (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ከነአን ማርክነህ (መቻል) ፣ ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ) ፣ በዛብህ መለዮ (ፋሲል ከነማ) ፣ መስኡድ መሐመድ (ጅማ አባ ጅፋር)

አጥቂዎች : ቸርነት ጉግሳ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል (ቅዱስ ጊዮርጊስ) ፣ ዳዋ ሆቴሳ (አዳማ ከተማ) ፣ ብሩክ በየነ (ኢትዮጵያ ቡና) ፣ በረከት ደስታ (መቻል) ፣ ይገዙ ቦጋለ (ሲዳማ ቡና)