ወደ ታንዛኒያ የሚያቀናው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ልዑክ ቡድን ዝርዝር ታውቋል

የሴካፋ ዞን የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የማጣሪያ ውድድር ለማድረግ ከነገ በስትያ ወደ ዳሬ ሰላም የሚያቀናውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስብስብ ሶከር ኢትዮጵያ አግኝታለች።

ለሁለተኛ ጊዜ በሚደረገው የአፍሪካ ሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የቀጠናውን የማጣሪያ ውድድር ለማድረግ እየተዘጋጀ የሚገኘው የወቅቱ የሊጉ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከነገ በስትያ ሀሙስ ረፋድ 4 ሰዓት ወደ ታንዛኒያ የሚያቀና ይሆናል። ቡድኑም በአዳማ ጄ ሪዞርት መቀመጫውን በማድረግ ልምምዱን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ሶከር ኢትዮጵያም ወደ ስፍራው የሚያቀናውን የቡድኑን ልዑክ ዝርዝር አግኝታለች። 20 ተጫዋቾች፣ 6 የአሠልጣኝ ቡድን አባላት እና 4 የአስተዳደር አባላት ወደ ስፍራው እንደሚያቀኑም ታውቋል።

ግብ ጠባቂዎች

ታሪኳ በርገና (22)
ንግስቲ መዓዛ (18)

ተከላካዮች

ሀሣቤ ሙዑዝ (4)
ትዝታ ኃይለሚካኤል (5)
እፀገነት ብዙነህ (16)
ብዙዓየው ታደሠ (15)
ጥሩአንቺ መንገሻ (2)
ናርዶስ ጌትነት (19)
ብርቄ አማረ (3)

አማካዮች

እመቤት አዲሱ (20)
ብርቱካን ገብረክርስቶስ (11)
ሰናይት ቦጋለ (21)
ትዕግስት ያደታ (8)
ታሪኳ ደቤሶ (17)
መሳይ ተመስገን (24)

አጥቂዎች

ሎዛ አበራ (10)
አረጋሽ ካልሳ (12)
መዲና ዐወል (9)
ፀጋነሽ ወራና (23)
አርያት ኢዶንግ (13)

የአሠልጣኝ ቡድን አባላት

ዋና አሠልጣኝ – ብርሃኑ ግዛው
ምክትል አሠልጣኝ – ኤርሚያስ ዱባለ
የግብ ጠባቂዎች አሠልጣኝ – ንጉሴ ወልደአማኑኤል
የህክምና ባለሙያ – ቃልኪዳን ዘገየ
ፊዚዮቴራፒ – ስንታየሁ ተሾመ
ቡድን መሪ – ተሾመ መተኪያ

የቡድኑ አንደኛ አምበል ሎዛ አበራ ስትሆን ትዝታ ኃይለሚካኤል ደግሞ ሁለተኛ አምበል ሆና ተመርጣለች።