የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላለፍ ታውቋል

10 ሰዓት ላይ ከዋሪየርስ ኩዊን ጋር የሴካፋ የቻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን የሚያደርገውን የንግድ ባንክ አሰላለፍ አግኝተናል።

በአሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚመራው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሊጉ አሸናፊ መሆኑን ተከትሎ በታንዛኒያ አስተናጋጅነት በሚከናወነው የሴካፋ ዞን የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ላይ እንደሚካፈል ይታወቃል። ቡድኑም 10 ሰዓት ላይ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከዛንዚባሩ ዋሪየርስ ኩዊን ጋር ያደርጋል። ሶከር ኢትዮጵያም የቡድኑን ቀዳሚ አሰላለፍ አግኝታለች።

ግብ ጠባቂ

ታሪኳ በርገና

ተከላካዮች

ናርዶስ ጌትነት
ትዝታ ኃይለሚካኤል
ሀሣቤ ሙሶ
እፀገነት ብዙነህ

አማካዮች

መሳይ ተመስገን
እመቤት አዲሱ
ሰናይት ቦጋለ

አጥቂዎች

መዲና ዐወል
ሎዛ አበራ
አረጋሽ ካልሳ

ያጋሩ