የጣና ሞገዶቹ ከአማካይ ተጫዋቻቸው ጋር በስምምነት ተለያይተዋል

ቡርኪናፏሳዊው አማካይ ከባህር ዳር ከተማ ጋር በስምምነት መለያየቱ ተረጋግጧል።

የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ለመጀመር የህክምና ምርመራ ለማድረግ በዛሬው ዕለት ተጫዋቾቹ በመሰባሰብ ላይ የሚገኙለት ባህር ዳር ከተማ ከአማካይ አብዱልከሪም ኒኪማ ጋር በስምምነት መለያየቱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ከአራት ዓመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ጥሩ ዓመት በማሳለፍ ከፈረሰኞቹ ጋር ከተለያየ በኋላ ጋንድዛሳር ካፓን ለተባለ የአርሜንያ ክለብ ፊርማውን በማኖር የተጫወተው ኒኪማ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ለጣና ሞገደቹ ከተጫወተ በኋላ አንድ ዓመት የሚያቆየው ቀሪ ኮንትራት እየቀረው ነው በስምምነት የተለያየው።

በሌላ ዜና ባህር ዳር ከተማ በቅርቡ አንድ የውጪ ሀገር ዜግነት ያለው ግብ ጠባቂ ለማስፈረም መቃረቡን ለማወቅ ችለናል።

ያጋሩ