ዛምቢያ 2017፡
ከ20 አመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ 1ኛ ዙር ማጣርያ ትላንት በተደረገ ጨዋታ ተጀምሯል፡፡ የመጀመርያ ጨዋታዎችም እስከ ነገ ይቀጥላሉ፡፡
በነገው እለት ከሚካሄዱ ጨዋታዎች አንዱ የሆነው የሱዳን እና ኬንያን ጨዋታ ኢትዮጵያውያን ዳኞች እንዲመሩት ካፍ መርጧቸዋል፡፡
በኦምዱርማኑ የኤል-ሜሪክ ስታድየም የሚደረገውን ጨዋታ ብሩክ የማነብርሃን በዋና ዳኝነት ሲመራ ትግል ግዛው እና ሽዋንግዛው ተባባል በረዳት ዳኝነት ጨዋታውን ይመራሉ፡፡
የአንደኛው ዙር ጨዋታዎች
(በመጀመርያ የተፃፉት በሜዳቸው የሚጫወቱ ናቸው)
አርብ መጋቢት 23 ቀን 2008
ቱኒዚያ 3-0 ኒጀር
ቅዳሜ መጋቢት 24 ቀን 2008
ሞዛምቢክ 1-0 ሞሪሸስ
ሩዋንዳ 1-1 ዩጋንዳ
ቡሩንዲ – ዲ.ሪ. ኮንጎ (ኮንጎ ራሷን ከውድድሩ በማግለሏ ቡሩንዲ ወደ ተከታዩ ዙር አልፋለች)
አንጎላ – ቻድ (ቻድ ራሷን ከውድድሩ በማግለሏ አንጎላ ወደ ተከታዩ ዙር አልፋለች)
ሴራልዮን ከ ጋምቢያ
ስዋዚላንድ ከ ናሚቢያ
እሁድ መጋቢት 25 ቀን 2008
ኢትዮጵያ ከ ሶማልያ
ላይቤርያ ከ ጊኒ
ዚምባብዌ ከ ቦትስዋና
አልጄርያ ከ ሞሪታንያ
ሱዳን ከ ኬንያ
ፎቶ – በ2015 የውድድሩ አሸናፊ ዛምቢያ