መቻል ግብ ጠባቂ አስፈርሟል

በዝውውር መስኮቱ የነቃ ተሳትፎ ያደረገው መቻል ከሲዳማ ጋር በስምምነት የተለያየውን የግብ ዘብ የግሉ አድርጓል።

በቀጣዩ ዓመት በአሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመራው መቻል በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን እያስፈረመ እንደሚገኝ ይታወቃል። ከደቂቃዎች በፊትም ተክለማርያም ሻንቆን በአንድ ዓመት ውል ማስፈረሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሲዳማ ቡና ያሳለፈው ግብ ጠባቂው ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እያለው ከክለቡ ጋር በስምምነት እንደተለያየ በትናንትናው ዕለት ዘግበን ነበር። የቀድሞ የሀላባ፣ አዲስ አበባ እና ሀዋሳ ከተማ ተጫዋች የእግር ኳስ ህይወቱን በጦሩ ቤት ለመቀጠልም ፊርማውን አኑሯል።

ያጋሩ