ለ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት የተጫዋቾች ጥሪ ተደረገ

እስካሁን ዋና አሠልጣኙን በይፋ ያላሳወቀው የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ላለበት የማጣርያ ጨዋታ ዝግጅት ለ35 ተጫዋቾች ጥሪ አስተላልፏል።

በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው ከ23 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ውድድር ድልድል ባለፈው ሳምንት መውጣቱ የሚታወስ ሲሆን ኢትዮጵያ በመጀመርያው ዙር ማጣርያ መስከረም ወር ላይ ኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክን የምትገጥምበት መርሐ ግብር አንዱ ነው። ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ቡድኑን የሚያሰለጥኑ አሠልጣኝ ይፋ ባያደርግም ለዚህ የደርሶ መልስ ጨዋታ ዝግጅት ይረዳ ዘንድ ለ35 ተጫዋቾች ጥሪ ማስተላለፉን በድረ-ገፁ ይፋ አድርጓል።

ግብ ጠባቂዎች

አላዛር ማርቆስ – ሀዋሳ ከተማ
አቡበከር ኑራ – ኢት. መድን
ፋሲል ገ/ሚካኤል – ባህር ዳር ከተማ

ተከላካዮች

መላኩ ኤልያስ – አርባ ምንጭ ከተማ
ኃይለሚካኤል አደፍርስ – ኢትዮጵያ ቡና
ብርሃኑ በቀለ – ሀዲያ ሆሳዕና
ዓለምብርሃን ይግዛው – ፋሲል ከነማ
ረመዳን የሱፍ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
እያሱ ለገሰ – ድሬድዋ ከነማ
አሸናፊ ፊዳ – አርባ ምንጭ ከተማ
መልካሙ ቦጋለ – ወላይታ ዲቻ
አሰጋኸኝ ጴጥሮስ – ድሬድዋ ከተማ
ሚሊዮን ሰለሞን – አዳማ ከነማ
አማኑኤል ተርፉ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

አማካዮች

አስጨናቂ ጸጋዬ – ኢትዮጵያ መድን
እንዳልካቸው መስፍን – አርባ ምንጭ
ቡቃታ ሸመና – አርባ ምንጭ
አብዱልከሪም ወርቁ – ኢትዮጵያ ቡና
ወንድማገኝ ኃይሉ – ሀዋሳ ከተማ
አበባየሁ ሀጂሶ – ወላይታ ዲቻ
ብዙአየሁ ሰይፈ – ወልቂጤ ከነማ
ከነአን ማርክነህ – መከላከያ

አጥቂዎች

ዱሬሳ ሹቢሳ – ባህር ዳር ከተማ
ጫላ ተሺታ – ኢትዮጵያ ቡና
ናትናኤል ገ/ሚካኤል – ፋሲል ከነማ
እዮብ ዓለማየሁ – ሀዋሳ ከነማ
መሀመድ ኑር ናስር – ኢትዮጵያ ቡና
አዲሱ አቹላ – መከላከያ
ተሾመ በላቸው – መከላከያ
መስፍን ታፈሰ – ኢትዮጵያ ቡና
አቡበከር ናስር – ማሜሎዲ ሰንዳውንስ/ደቡብ አፍሪካ

አህመድ ሁሴን – አርባ ምንጭ ከተማ
ይገዙ ቦጋለ – ሲዳማ ቡና
ብሩክ በየነ – ኢትዮጵያ ቡና
ፍቃዱ ዓለሙ – ፋሲል ከነማ