ፈረሰኞቹ አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታን ዋና አሰልጣኝ አድርገው ሾመዋል

በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ፈረሰኞቹን በጊዜያዊነት እየመሩ የቆዮት አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ በመሆን ተሹመዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ለ2014 የውድድር ዘመን ዝግጅት በጀመረበት ወቅት ሰርቢያዊውን አሰልጣኝ ዝላትኮ ክራምፓቲችን በዋና አሰልጣኝነት ቢሾምም አሰልጣኙ ከተጫዋቾች ጋር የነበረባቸው የተግባቦት ችግር ተከትሎ የክለቡ አመራር አሰልጣኙን በማሰናበት አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ ቡድኑን በጊዜያዊነት እንዲመሩ መደረጉ አይዘነጋም።

አሰልጠኝ ዘሪሁን ቡድኑን በሀላፊነት በመሩባቸው ጨዋታዎች በአንዱ ጨዋታ ብቻ ሽንፈት ያስተናገዱ ከመሆናቸው ባሻገር ፈረሰኞቹ ከአራት አመት በኋላ አስራ አምስተኛ ዋንጫቸውን እንዲያነሱ አስችለዋል ፤ ይህን ተከትሎ የክለቡ ሥራ አመራር ቦርድ አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን ክለቡ ይፋ አድርጓል።