መቻል በአማካይ እና ተከላካይ ቦታ የሚጫወት ተጨዋች አስፈርሟል

በአሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመራው መቻል ተጨማሪ ተጫዋች ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

የቀድሞ ስሙን መቻል ዳግም ያገኘው የሊጉ ክለብ በቀጣዩ ዓመት በሊጉ ተፎካካሪ ለመሆን ከአሠልጣኝ ቅጥር ጀምሮ በርካታ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም ሰንብቷል። በአሁኑ ሰዓት ቢሾፍቱ ላይ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን እያደረገ የሚገኘው ክለቡም በዛሬው ዕለት የተከላካይ እና አማካይ መስመር ተጫዋች ማስፈረሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ክለቡን የተቀላቀለው ተጫዋች የአብስራ ሙሉጌታ ነው። ከቅዱስ ጊዮርጊስ የታዳጊ ቡድን የተገኘው የአብስራ ምንም እንኳን ዋና ቡድኑን በወጥነት ባያገለግልም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ጅማ አባ ጅፋርን ተቀላቅሎ በሀገሪቱ ከፍተኛ የሊግ እርከን ሲጫወት ነበር። አሁን ደግሞ የእግርኳስ ህይወቱን በጦሩ ቤት ለመቀጠል የአንድ ዓመት ውል ፈርሟል።

ያጋሩ