ጋናዊው የመሀል ተከላካይ ብርቱካናማዎቹን ተቀላቅሏል

ድሬዳዋ ከተማ በመሀል ተከላካይ ቦታ ላይ የውጪ ሀገር ዜጋ ተጫዋች አስፈርሟል።

በአሰልጣኝ ዮርዳኖስ አባይ እየተመሩ መጪውን አዲስ የውድድር ዘመን የሚጀምሩት ድሬዳዋ ከተማዎች ቡድናቸውን በአዳዲስ ተጫዋቾች ሲያጠናክሩ ቆይተዋል። ክለቡ ማምሻውን ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት ደግሞ ጋናዊው የመሀል ተከላካይ አሳንቴ ጋድፍሬድ የቡድኑ አዲስ ፈራሚ ሆኗል።

በሀገሩ ጋና አሻንቲ ኮቶኮን ጨምሮ ለአራት ክለቦች ተጫውቶ ያሳለፈው ተከላካዩ በጊኒው ሆሮያም ቆይታ ነበረው። ተጫዋቹ በአንድ ዓመት ውል ወደ ድሬዳዋ መምጣቱን ክለቡ ጨምሮ ገልጿል።

ያጋሩ