ሀድያ ሆሳዕና የአማካይ ስፍራ ተጫዋች አስፈርሟል

በሆሳዕና ከተማ ሲደረግ በነበረው የክረምት (ያሆዴ ዋንጫ) ውድድር ላይ የታየው አማካይ ከቤራዎቹን ተቀላቅሏል።

አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹን እስካሁን በይፋ መሾማቸውን ያልገለፁት ሀድያ ሆሳዕናዎች ቤዛ መድህን ፣ ዳግም በቀለ ፣ ሰመረ ሀፍታይ ፣ እንዳለ ደባልቄ ፣ አክሊሉ ዋለልኝ ፣ ዘካሪያስ ፍቅሬን ፣ ፔፕ ሰይዱ ፣ ሪችሞንድ ኦዶንጎ ፣ ስቴፈን ናያርኮን እና በትላንትናው ዕለት መለሰ ሚሻሞን አስፈርመው የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የቀጠሉ ሲሆን አሁን ደግሞ ተጨማሪ ተጫዋች በሁለት ዓመት ውል የስብስቡ አካል አድርገዋል፡፡

የቡድኑ አሠልጣኝ በሆሳዕና ከተማ ሲደረግ የነበረው የክረምት (ያሆዴ ዋንጫ) ውድድር የተመለከቱትን ሲሆን በውድድሩም መልካም እንቅስቃሴ አድርጓል ብለው ያመኑትን አማካዩ ብሩክ ማርቆስን ማስፈረማቸው ታውቋል።

ያጋሩ