“የአፍሪካ እግርኳስ ያለበትን ደረጃ ለማሳየት እንሞክራለን” ፍሎራ ኢቤንጌ

ነገ 10 ሰዓት የሀገራችንን የቻምፒየንስ ሊግ ተወካይ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚገጥመው የአል-ሂላል አሠልጣኝ ፍሎራ ኢቤንጌ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ቆይታ አድርገዋል።

ዝግጅት እንዴት ነበር?

“በጣም ጥሩ ነበር ፤ 7 የሚጠጉ ተጫዋቾች በብሔራዊ ቡድን ስለነበሩ ትንሽ ፈታኝ አድርገውብናል ፤ ከአንድ ሳምንት በፊት ነበር ቡድኑን የተቀላቀሉት። ይህም የቡድኑን ውህደት ለማምጣት አስቸግሮናል። እኛ አናማርርም ፤ ቢሆንም ጠንካራውን ቅዱስ ጊዮርጊስን እንገጥማለን።”

ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያላቸው መረጃ…?

“ጥሩ ቡድን እንደሆነ አውቃለሁ። ከጥቂት አመታት በፊት ከቪታ ጋር ሆኜ ቅዱስ ጊዮርጊስን ገጥሜ ተሸንፍያለሁ።  ጨዋታው የደርሶ መልስ ነው። ከሁለቱ ጨዋታዎች በኋላ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ የተቻለንን ጥረት በጥንቃቄ እናደርጋለን።”

ከቡድን ዜና ጋር በተያያዘ…?

“ስለዚህ ጉዳይ ማውራት አልፈልግም። ሁሉም ይዘናቸው የመጣናቸው ተጫዋቾች የተቻላቸውን እንዲያደርጉ እፈልጋለሁ።”

ከነገው ጨዋታ ምን እንጠብቅ?

“ጥሩ ኳስ እንደምናሳይ ተስፋ አደርጋለሁ ፤ የአፍሪካ እግርኳስ ያለበትን ደረጃ ለማሳየት እንሞክራለን። ሁለቱም ቡድኖች የተሻለ ነገር ለማሳየት ይሞክራሉ ብዬ እጠብቃለሁ።”