አመሻሽ ላይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የተፋለመው የሱዳኑ ክለብ አል-ሂላል አሠልጣኝ ፍሎረንት ኢቤንጌ የድህረ-ጨዋታ አስተያየት ሰጥተውናል።
ጨዋታው እንዴት ነበር…?
ቀላል ጨዋታ አልነበረም። ምክንያቱም በመጀመሪያው አጋማሽ ሁለት ስህተቶችን ፈፅመን ነበር። ስህተቶቹን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግብ አስቆጥሯል። በእረፍት ሰዓት የተወሰኑ ለውጦችን ለማድረግ ሞክረናል። በዚህም በሁለተኛው አጋማሽ እኛ የተሻልን ነበርን። ዕድለኛም ነበርን አንድ ጎል አስቆጥረናል። እርግጥ ጨዋታውን አላሸነፍንም ፤ ግን ካርቱም ላይ የመልስ ጨዋታ አለን።
በሁለተኛው አጋማሽ ስለነበራቸው ብልጫ…?
ልክ ነው። በሁለተኛው አጋማሽ ከመጀመሪያው የተሻልን ነበርን። ከዚህ ጨዋታ መማር ይገባናል። የሰራናቸውን ስህተቶችም በደንብ ማየት እና ማስተካከል ያስፈልገናል። ከወዳጅነይ ጨዋታዎች ውጪ ይሄ ገና የመጀመሪያ የነጥብ ጨዋታችን ነው። ይሄ የአህጉራችን ትልቁ ውድድር ነው። ስለዚህ ከዛሬው የበለጠ ለቀጣይ መስራት ይገባናል።
ስለመልሱ ጨዋታ…?
የመልሱ ጨዋታ ፈታኝ ነው የሚሆነው። ምክንያቱም ቅዱስ ጊዮርጊስ ጥሩ ቡድን ነው። ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ዛሬ ከሰራነው በላይ ለመልሱ ጨዋታ መስራት ይገባናል።
ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ስላላቸው ዕድል…?
እየሰራን ያለነው ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ነው። በእርግጠኝነትም ወደ ቀጣዩ ዙር እናልፋለን።