ጋምቢያዊው አጥቂ ለነገው ጨዋታ ይደርሳል

ፋሲሎችን የተቀላቀለው አዲሱ ፈራሚ ለነገው ጨዋታ የመድረሱ ነገር ተረጋግጧል።

ነገ ባህር ዳር ላይ በሚደረገው የኮፌዴሬሽን ካፕ ፍልሚያ አስቀድሞ ባደረስነው ዘገባ በፋሲል ከነማ በኩል በጉዳት ምክንያት ሀብታሙ ተከስተ ከጨዋታው ውጪ መሆኑ ሲረጋገጥ አዲስ ፈራሚው ጋምቢያዊው አጥቂ ጋይራ ጁፍ የመኖርያ ፍቃድ ያላለቀለት በመሆኑ ለነገው ጨዋታ የመድረሱ ነገር ያልተረጋገጠ እንደሆነ ገልፀን ነበር።

ሆኖም አሁን ከክለቡ ባገኘነው መረጃ መሰረት ተጫዋቹ የመኖርያ ፍቃድ ማግኘቱ የተረጋገጠ ሲሆን የተለየ ነገር ካልተፈጠረ በቀር ለነገው ጨዋታ ዝግጁ መሆኑ ተገልፆልናል።

ያጋሩ