በአዳማ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅት እየሰሩ የሚገኙት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ሙከራ ሰጥተውት የነበረውን አማካይ አስፈርመዋል፡፡
በአሰልጣኝ ክፍሌ ቦልተና መሪነት የበርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር ፈፅመው ከነባሮቹ ጋር በማዋሃድ በአዳማ ከተማ መቀመጫቸውን አድርገው ዝግጅታቸውን እየሰሩ የሚገኙት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች የመጨረሻ ፈራሚያቸውን በእጃቸው አስገብተዋል፡፡ በአማካይ ስፍራ ላይ ሲጫወት የምናውቀው ሔኖክ አንጃ የተሰጠውን የሙከራ ዕድል በአግባቡ በመጠቀሙ አዲሱ የኤሌክትሪክ ፈራሚ የሆነው ተጫዋች ነው፡፡
መነሻውን ከአዳማ ከተማ ያደረገው እና በሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ፣ አዲስ አበባ ከተማ ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ እንዲሁም የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በገላን ከተማ ያሳለፈው ወጣቱ አማካይ በአንድ ዓመት ውል ኤሌክትሪክን መቀላቀል ችሏል፡፡