ወደ ካርቱም የሚያቀኑት የፈረሰኞቹ ተጫዋቾች ታውቀዋል

በዚህ ሳምንት መጨረሻ በአፍሪካ ቻሚፒየንስ ሊግ የመልስ ጨዋታቸውን የሚከውኑት ፈረሰኞቹ ወደ ሱዳን ተጓዥ ተጫዋቾቻቸው ተለይተዋል።

በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታቸውን ከቀናት በፊት በባህር ዳር ስታዲየም የሱዳኑን አል ሂላል ኡምዱሩማንን 2-1 በሆነ ውጤት ፈረሰኞቹ ማሸነፋቸው ይታወሳል።

የፊታችን እሁድ መስከረም ስምንት ደግሞ በሱዳንዋ መዲና ካርቱም ከተማ ላይ ለሚኖራቸው የመልስ ጨዋታ ዛሬ ከዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ለሁለት ሰዓት የዘለቀ ጠንካራ ልምምድ በክቡር ይድነቃቸው ተሰማ አካዳሚ ሰርተው ፤ በዚህም ልምምድ ላይ በመጀርያው ጨዋታ ጉዳት ያስተናገደው ቸርነት ጉግሳ ከቡድኑ ጋር በመልካም ጤንነት ልምምዱን ሲሰራ ተመልክተናል።

ነገ ረፋድ ላይ ወደ ካርቱም የሚያቀኑት ቅዱስ ጊዮርጊስ ይዘዋቸው የሚጓዙትን የ20 ተጫዋቾችን ዝርዝር ሶከር ኢትዮጵያ አግኝታለች።

በዚህም

ግብጠባቂ

ቻርልስ ሉክዋጎ፣ ባህሩ ነጋሽ

ተከላካይ

ምኞት ደበበ፣ ኤድዊን ፊሪምፖንግ፣ ሄኖክ አዱኛ፣ አማኑኤል ተርፋ፣ ረመዳን የሱፍ፣ ደስታ ደሙ፣ ሱሌማን ሐምዲ

አማካይ

ናትናኤል ዘለቀ፣ ጋቶች ፓኖም፣ በረከት ወልዴ፣ ሀይደር ሸረፋ፣ ዳዊት ተፈራ፣ ቢንያም በላይ፣ ቸርነት ጉግሳ፣ ዳግማዊ አርአያ፣ አብርሀም ጌታቸው፣

አጥቂ

ኢስማኤል ኦሮ አጎሮ፣ ተገኑ ተሾመ መሆናቸው ታውቋል።

ከስብስቡ ጋር ልምምድ ሲሰሩ የሰነበቱት የተቀሩት አምስት ተጫዋቾች ደግሞ ከሌሎች የዕድሜ ዕርከን ከተውጣጡ ተጫዋቾች ጋር በመጪው ቅዳሚ በሚጀምረው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ቡድኑን ወክለው የሚሳተፉ ይሆናል።

በተያያዘ ዜና ጠዋት ባቀረብነው መረጃ መሰረት ቅዱስ ጊዮርጊስ ለካፍ በላከው ደብዳቤ ጨዋታው በገለልተኛ ሜዳ እንዲካሄድ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ስለማግኘቱ የተረጋገጠ ነገር ባለመኖሩ ነገ ወደ ሱዳን የመሄዳቸው ነገር እርግጥ ሆኗል።

ያጋሩ