የጣና ሞገዶቹ የግብ ዘብ የብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦለታል

በቅርቡ ባህር ዳር ከተማን የተቀላቀለው የግብ ዘብ ለብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦለት ወደ ፈረንሳይ አቅንቷል።

አንድ ሜትር ከዘጠና ሁለት ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው አይቮሪኮስታዊው ኤሊዘር ኢራ ቴፕ በቅርቡ ባህር ዳር ከተማን መቀላቀሉ ይታወቃል። በትናትናው ዕለት በጣና ሞገዶቹ መለያ የመጀመርያ ጨዋታውን ያደረግ የግብ ዘቡ ከጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ ለሀገራዊ ግዳጅ ወደ ፈረንሳይ ማቅናቱ ታውቋል።

ግብ ጠባቂው በፊፋ ካሌንደር መሠረት ነገ አይቮሪኮስት ከጊኒ እንዲሁም እሁድ ከቶጎ ጋር በፈረንሳይ ለምታደርገው ጨዋታ ነው ጥሪ ቀርቦለት የተጓዘው። ኤሊዘር ቴፕ ከዚህ ቀደም በሀገሩ የኦሎምፒክ ቡድን እና ዋናው ብሔራዊ ቡድን ተሳትፎ መጫወቱ ይታወሳል።

ያጋሩ