“ጨዋታውን ኪንሻሳ ላይ እንጨርሰዋለን ብዬ አስባለሁ” አሰልጣኝ ኪሞቶ ፒፓ

ያለግብ ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኋላ የዲ. ሪፐብሊክ ኮንጎ አሰልጣኝ ኃሳባቸውን አጋርተዋል።

ስለውጤቱ…

“ውጤቱ በጣም ጥሩ ነው ፤ ተጫዋቾቼ ጥሩ አድርገዋል። ጨዋታውን ኪንሻሳ ላይ እንጨርሰዋለን ብዬ አስባለሁ።”

ስለጨዋታ ዕቅዳቸው…

“የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ወደኛ እስኪመጡ መጠበቅ እና ኳሱን ስናገኝ በፍጥነት  ወደፊት መሄድ ነበር ዕቅዳችን። መስመሮቹን መዝጋት ነበር የፈለግነው። ኪንሻሳ ጥሩ እንጫወታለን ብዬ አስባለሁ።”

ስለዳኝነቱ…

“ስለ ዳኞች ማውራት አልፈልግም ፤  አፍሪካ ውስጥ ነው ያለነው። ቡድናችን ላይ ነው ትኩረት የማደርገው እና ቡድናችንም በጣም ጥሩ ተጫውቷል። በመልሱ ጨዋታ በጣም ጥሩ እንጫወታለን ብዬም አስባለሁ ፤ እና ከዳኞች ምንም አልጠብቅም። ሁሉም ሥራውን ነው የሚሠራው እኛም ሥራችን ላይ እናተኩራለን ጠንክሮ የሰራ ደግሞ ጥሩ ውጤት ያገኛል።”

ስለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን…

“የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በጣም ጥሩ ቡድን ነው ፤ አድንቄያቼዋለሁ። መስመሮቹን ዘግተን ለመጫወት ሞክረናል። የመጀመሪያው አጋማሽ ለኛ ጥሩ ነበር አንድ ሁለት የግብ ዕድሎች ነበሩን ግን ይሄ እግርኳስ ነው። ለመዘጋጀት አራት ቀናት አሉን ጨዋታው ገና አላለቀም። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሩ ነው ለእነሱ ጥሩ ስሜት ነው ያለኝ። የመልሱን ጨዋታ ደግሞ ኪንሻሳ ላይ የምናየው ይሆናል።”