የፈረሰኞቹ አጥቂ ከሀገሩ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦለታል

ቶጎ ነገ ላለባት የወዳጅነት ጨዋታ ለቅዱስ ጊዮርጊሱ አጥቂ ጥሪ በማቅረቧ ተጫዋቹ ወደ ፈረንሳይ አምርቷል፡፡

የተጠናቀቀውን የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሊጉን ዋንጫ ከፍ በማድረግ ያነሳው አጥቂው ኢስማኤል ኦሮ – አጎሮ ቶጎ ላለባት የወዳጅነት ጨዋታ ለሀገሩ ጥሪ ቀርቦለት ወደ ፈረንሳይ አምርቷል፡፡ ነገ ረፋድ 4፡00 ሰዓት ላይ ፈረንሳይ ፓሪስ በሚገኘው ሮበርት ዲዮኮን ስታዲየም ከአይቮሪኮስት ጋር ሀገሪቱ በምታደርገው የወዳጅነት ጨዋታ ላይ ተጫዋቹ ግልጋሎት ለመስጠት ነው በትላንትናው ዕለት ብሔራዊ ቡድኑን በመቀላቀል ልምምድ የጀመረው፡፡

የአሰልጣኝ ፓውሎ ዱዋርቴዋ ቶጎ በቀጣዮቹ ቀናትም የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ማቀዷ የተነገረ ሲሆን አጎሮ ሁሉ ባህርዳር ከተማን በክረምቱ የተቀላቀለው አይቮሪኮስታዊው ግብ ጠባቂው ኤሊዘር ኢራ ቴፕም ለሀገሩ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦለት ወደ ፓሪስ ማምራቱም ይታወሳል፡፡

ያጋሩ